Faith Statement
መሰረታዊ የክርስትና እምነት አቋም
መሰረታዊ የክርስትና እምነት አቋም
1. ሁሉን በሚችል ፍፁም በሆነ ሰማይና ምድርን እንዲሁም በውስጧ ያሉትን ሁሉ በፈጠረና በሚገዛ ለዘላለም በአንድነትና በሶስትነት በሚኖር በእግዚአብሔር አብ፤በእግዚአብሔር ወልድ ና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ /ስላሴ/ እናምናለን፡፡ማቴ 28፡-19 ዮሀ 17፡-3 ቆሮ13፡-14
2. ስልሳ ስድስቱን የብሉይና የአዲስ ኪዳን መፃህፍትን የያዘው መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ተጠቅሞ የተፃፈ ምንም ስህተት የሌለበት እግዚአብሔር እራሱን ለሰው ልጆች ደህንነት የገለፀበት የማይጨመርበት፤ የማይቀነስበት ብቸኛና የመጨረሻ ስልጣን ያለው በፅሁፍ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነና ለአማኞች እምነትና ኑሮ አዛዥ ፤መሪና ባለሙሉ ስልጣን መሆኑን እናምናለን፡፡2ጢሞ 3፡16-17 2ጴጥ 1፡19-21
3. በመፍጠር፤ ፍጥረትን በመጠበቅና ፍጥረትን በማስተዳደር በመዋጀት በመጨረሻው ፍርድ የእግዚአብሔር ፍፁም ስልጣንና ሉዓላዊነት እናምናለን፡፡ ሮሜ -16 ኤፌ
4. ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም የአብ የባህሪ ልጅ መሆኑን፤ ከአብ የተላከ መሆኑን፤ ፍፁም ሰውና ፍፁም አምላክ መሆኑን፤ ከመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም የተወለደ፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ጢያት ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞተ፤በተቀበረ ወደ ሲኦል በወረደ፤በሶስተኛውም ቀን በስጋ በሞት በተነሳ ወደ ሰማይ ባረገ፤ አሁን ሊቀካህናችንና ጠበቃችን ሆኖ በአባቱ ቀኝ ባለ፤ተመልሶ በክብርና በግርማ በሚመጣ በአብ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡ ማቴ ዮሀ ሐዋ ዕብ
5. መንፈስ ቅዱስ ፍፁም አምላክ እንደሆነና ክርስቶስን እንደሚያከብር ሰዎችን ስለ ሀጢያት በመውቀስ ዳግም እንዲወለዱ በሚያደርግ፤ በአማኞች ውስጥ በሚኖር እውነትን በሚያስተምርና በሚመራ፤ ለተቀደሰም ኑሮና አገልግሎት በሀይሉ በሚያስታጥቅ፤ በስጦታዎቹም በሚሞላ፤ ህልውና ያለው አካላዊ መንፈስ በሆነው መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ልዩ ልዩ የፀጋ ስጦታዎችን በማካፈል፤ ድውዮችን በመፈወስ፤ አጋንንትን በማስወጣትና ተዓምራትን በማድረግ ዛሬም ህያው ሆኖ እንደሚሰራ እናምናለን፡፡
6. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን፤ በሀጢያት የወደቀና የጠፋ በዚህም ምክኒያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የጌታ ኢየሱስን የመስቀል ላይ ስራ አምኖ በመቀበል ዳግም ልደትንና ድህነትን እንዲሁም ህያው ሆነ መንፈሳዊ ህይወትን እንደሚያገኝና በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት በመሆን መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ እንደሚሰራ እናምናለን፡፡
7. ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሚያገለግሉና በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው በተለይም አማኞችን ከእግዚአብሔር ተልከው እንደሚረዱ እናምናለን፡፡ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ። ዕብ 1:14 መዝ 91:11
8. ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ አምኖ ሌሎችን መላእክት አሳምኖ ከእግዚአብሔር ክብር ፊት የተጣለ የሀሰት ሁሉ አባት፤የሀጢያት ሁሉ ምንጭ እንደሆነና አብረውት የወደቁት ርኩሳን መናፍስትም ስራቸው ዘወትር ክፉ እንደሆነና በተጨማሪም የእግዚአብሔርና የሰው ልጆችም ሁሉ ጠላቶች እንደሆኑ እናምናለን፡፡ ኢሳ 14 ራእይ -9
9. ሰው በመልካም ስራው ሳይሆን ሀጢያቱን ተረድቶና ወንጌልን ሰምቶ የኢየሱስን ሞና ትንሳኤ የፅድቅና የደህንነት መንገድ መሆኑን አምኖና ይህንን በእምነት ተቀብሎ ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዶ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሆንና የዘላለምን ህይወት እንደሚወርስ እናምናለን፡፡ ሐዋ ሮሜ ሮሜ ቲቶ -7
10. መሰረቷና ራሷ ክርስቶስ በሆነ በጌታ በኢየሱስ የመቤዠት ስራ አምነው ድህነትን ተቀበሉ ሁሉ በሚገኙባት የክርስቶስ አካል በሆነች አንዲት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ የዚህችም የማትታየዋ ቤተክርስቲያን አባላት የሆኑቱ ብቻ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባላት መሆን እንደሚገባቸውና እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ኤፌ ኤፌ ቆላ
11. የውሃ ጥምቀት ስርዓት ቤተክርስቲያን የምታከናውነው፤ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰረት ዳግም የተወለዱ አማኞች ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበራቸውን ለመግለፅና ለመመስከር ሲሆን/ከኢየሱስ ጋር መሞታቸውንና ከእርሱም ጋር በአዲስ ህይወት መነሳታቸውን/ የጥምቀቱምስርዓት የሚፈፀመው በአብ፤ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ስም በውሃ ውስጥ በመጥለቅና በመውጣት መሆኑና እናምናለን፡፡ ማቴ -19
12. የጌታ እራት የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት እንድንሰብክ የሚያሳስበን በአማኞች መካከል መደረግ ያለበትየተቀደሰ ስርዓት እንደሆነና ከጌታና ከአማኞች ጋር ያለንንህብረት ለመግለፅ የሚደረግ የመታሰቢያ ስርዓት እንደሆነ እናምናለን፡፡ 1ቆሮ
13. ክርስቲያናዊ ጋብቻ በአንድ አቅመ አዳም በደረሰ አማኝ ወንድ እና በአንዲት ለአቅመ ሄዋን በደረሰች አማኝ ሴት መካከል የሚፈፀም የእድሜ ልክ ኪዳን እንደሆነ እናምናለን፡፡ በክቡር ጋብቻ መካከል ጋብቻን ማክበርና መንከባከብ እንደሚገባቸው እናምናለን፡፡ ሚል2 6.
14. አስራትና መባ እንዲሁም ስጦታዎችን በመስጠት ቤተክርስቲያንን ማገልገል እንዲሁም ድሆችን፤ መበልቶችን፤ አካለ ጎዶሎዎችን ሴተኛ አዳሪዎችን፤ የጎዳና ተዳዳሪዎችን እንዲሁም ወላጅ የሌላቸው ህፃናትን መርዳትና መንከባከብ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን፡፡ 1ቆሮ -14 6.
15. የአማኞች ሞት ማንቀላፋት አንደሆነ እናምናለን፡፡ጌታ እስኪመጣ ድረስ ህያው ሆነው የሚቀሩት ካለሆኑ በቀር ጌታ አንዳንዶቹን በራሱ ፈቃድ እንዲያንቀላፉ እንደሚያደርግ እናምናለን፡፡ 1ተሰ 6.
16. በሙታን ትንሳኤ እናምናለን፡፡ የሞቱ ሁሉ በስጋ ትንሳኤ ከሞት እንደሚነሱ የሚበሰብሰው አካል የማይበሰብስ ሆኖ እንደሚነሳና አማኞች ከጌታ ጋር ወደ ዘላለም በረከትና ደስታ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ የማያምኑት ዳግም ወደ ዘላለም ፍርድ እና ቅጣት እንደሚሄድ እናምናለን፡፡ ራዕይ 20 ዮሀ -29 1ቆሮ15 6.
17. ጌታ ዳግም ሲመጣ መንግስቱን በምድር ላይ እንደሚተክልና ሺህ አመት እንደሚገዛ የፊተኛውን ትንሳኤ ያገኙ ቅዱሳንም ከእርሱ ጋር በመሆን በሺህ አመቱ አገዛዝ እንደሚነሱ እናምናለን፡፡ ራዕይ -6 6.
18. አማኞች ከአለማዊነትና በአለም ከሚገኙት ከንቱ የስጋ ፍሬዎች ተለይተው ለቅድስና ኑሮ እንደተጠሩ እናምናለን፡፡ ሮሜ -2 2ቆሮ ቲቶ -14 1ኛ ዮሀ -17